FANDOM


ይድረስሽ ካለሁበት ለአንቺ....

እዉነትን ሰንቂ እዉነትን አንግቢ

ለገንዘብ ለስልጣን እዉነትን አትሺጪ

ስልጣንስ ገንዘብስ ወገንሽ መሆኑን እወቂ

የጥቁሮችን ዝና ሀይማኖት በነጭ ነጫጮች አትለዉጪ

ሀቅስ ታሪክ ነዉ.....

በአድዋ ምን ነበርን ማን ነበርን

ብለሽ 

ከቆዩ ከቆዩት ከጠየቅሽ ታገኛለሽ

ምላሽ


መፅሀፍ አልነበብ አለኝ።

አላነብም ባነብም ከሀሳቡ አልጣጣም

ደረሲዉ ሀያሲዉ፣ከሀቁ የማይጣጣም

እያወቅሁ ታዲያ እንዴት 

ዉሸት ላልም

በዚያ በረጂም ቃላቱ

ይደረድረዋል ስንቱን እንቶ ፈንቶ

ሀሳቡ ዉሸቱ በብር ጥማት ተጠምቶ

ይጨቀጭቃል ያንቆረቁራል እንቶፈንቶ

መፀሀፋ ለወግ ለህትመት በመብቃቱ።

አሰፈረዉ ሰብስቦሰባስቦ ዉሸትን ከቤቱ።

ደራሲስ...አለፋ....እየለፈለፍ

ይህን እንቶ ፈንቶ እንደነቀፍ


እንደ አዋቂ ሰዉ ሳይሆን

እንደህፃን በእጄ እየዳክሁ

....

እኔ ነኝ!

ህይወትን እየኖርሁ ሳይሆን

እንደ ህፃን እየዳክሁ

በእግሬ ሳይሆን በእጄ እየታገዝሁ የምገኝ፣የምኖር እኔ ነኝ።

እኔ....ነኝ.....

በዉሀ ላይ የምወራጭ የምኖር

ለመኖር ያልፀድቅሁ ያልተፈጠርሁ

የብስጭት መብቀያ ከስር ከስር

እኔ ነኝ

ህይወትን የማልኖር የማኗኑር።


ለወገኑ ነዉ?

ዶክተር መሀይሙ ሌት ከቀን

ክረምት ወይም በጋ

በሚሰራ ሰራ ወገረ ፈለጠን

ኢንጅነሩ እንደ አርማታ አቦካን

መሪዉን እደፈረስ ለጎመን

ቄስ ሸህ ተብዬ ተዘረፋብን

መኖር በነፃነት ቢያቅተን

ለብቻችን ለአምላክ ፀልየን

ቁጭት፣ብስጭት ባሰማን

ይህ ሁሉ የሚሰራዉ

ለወገኑ ነዉ ብለን።


የሰዉ ዝምድና

ልቸርችርህ ቢሉት የማይነገድ 

የህይወት አይነተኛ መንገድ

ዉሸትን ሳይሆን እዉነትን 

የሚያፀድቅ በጥልቀት የሚፈልግ 

የእዉነት መንገድ ነዉ

ከልብ ጠልቆ ለጠየቀዉ

የሰዉ...ዝምድናዉ....

መረዳዳት መደጋገፋ መጠያየቅ

መቀራረብ መተሳሰር ይልቅ

ዜመዴ ዘመድሽ ዘመዶቻችሁ

ብላችሁ ዘመድን ካልጠበቃችሁ

መቺ ዝምድናን ከባንክ ታገኙታላችሁ።


ድንጋይ

ንዴት፣ብስጭት፣ትቺት የማይገባዉ

ሁሉን የሚሰማዉ ቢሆን ንዴት በኖረዉ

ዛሬ ላይ ተናዶ ተናዶ ጭስ በሆነዉ

ድንጋይስ አበጀ...

የዘመኑ ሰዉ እንኮን ለገባዉ

ያልገባዉን ወቅሮ ቀጥቅጦ ያስገባዉ

የዛሬ ሰዉ ብዙ ነዉ መአቱ

ድንጋይ ሆነ ሰዉ በየለቱ

ድንጋዋች አምፀዉ....

ሰዉ በመራጃ ቢወቅር ቢቀጠቅጣቸዉ

አልሰበር አሉ በመፋቀራቸዉ።የመስቀል ወፍ

ምነዉ ዉዲቷ ወፌቱ መጥፍቷ

አስራሁለት ወር ጠፍታ ዛሬ መገኘቷ

ምንስ ጠፍቶ ነዋ ከቤት ከጎጆዋ

ያቺ በራሪዋ....

አደይ ሲፈካ ብቅ ትላለች

አመታት ወራትን ጠብቃ

ወረሀ መስከረምን ብቅ ትላለች

ከወሩ ጋር ከሌሎች ወፍ ተለይታ

ደምቃ፣ተዉባ በየሳሩ ላይ ትታያለች

እሷ....

የመስቀል ወፋ ነች ሁልዬ የማትተች

እሷም ቢፈቀድላት ሰዉ አትተች።
ሀገሬ

አንቺ ሀገር....

ስንቱን አባረርሽ አራቅሽዉ 

ስንቱንስ አፈር አስገባሽዉ

ስንቱንስ በየአስፖልቱ ደፍሽዉ

ስንቱንስ በየሰፈር ቸረቸርሺዉ

አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ

ብባልም በሀቁ....

ሀገር ሀገር መሆኑን እወቁ።ፍቅር

ፀሀፌዉ እያቆለጳጰሰ

እንዲህ ይላል....

ዳሌዋ ሲቆጣ

ቅንዝሩ ሲመጣ

አረ...

ምሷን ስጣት

ምንም አታመጣ

ፍቅርስ....

በብዙ ይገለፃል

ለምን...

እሷን እንላለን

ሀገርም ፋቅር አለዉ

የድሮዉን ዛሬ ባናየዉ።

አበባ

ሰዉ እንዴት ሳያፈራ

ወጣወጣ ያፈራል

ወጣወጣስ ላፈሩ

ይቸረችራሉ ያልረገፈ አበባቸዉን

ሸጠዉ ሸጠዉ ....

መጨረሻቸዉ ምን ይኮን

ያላበባ.....

ፋሬ ታይቶ አይታወቅም

የዛሬዉ የጉድ ነዉ

መጨረሻ ዉጤቱ የማይጥም

መቼም ቢሆን የማይጣጣም።የህይወት መንገድ

ብዙ ዉጣዉረድ የሞላበት

ከዛሬ ነገ ....

የእያንዳንዱ የህይወት ሰርጥ

እዉቀት ና ልብ የምገዛበት

የህይወት መንገድ ነዉ

በደንብ ላነበበና ላጠናዉ።

መንገዱ.....

ስርጣስርጥ...አቅበት የበዛበት

ካልበረታህ....

አላማ...ተስፍ የሚጨልሙበት

በጣም አስቸጋሪ መንገድ ነዉ

መርምሮ አጥንቶ ላወቀዉ።
የዘዉድ አልጋ

ድሮ በአፂዋቹ ዘመን

ገና ህይወት ንሮ ሳይዘምን

የዘዉዱ አልጋ አልረጋም 

ይባላል።

ጫጫታ ሁከታ ከተሰማ።ማዶ

በአይኔ ፈዝዤ በልቤ ነጉጄ

በርቀት እያየሁ ማዶ

መቼ ወደድሁ መኖር በደጄ

ማዶ ሆኗል የልቤ ወዳጄ

ዉዳሴ እያደረስኩ ከደጄ

ጨርሼ ልነሳ ስፋጨረጨር

ልቤ ጥሎኝ ጠፋ

ከኔለኔ ሳያስፈቅድ፣ሳይናገር

አገር ማ ማዶ...እላለሁ

አገር ግን በጄ ነበር 

መጥቀም፣መጠቀም ባላይም

ልቤን ማዶ ልኬ ዝም አልልም።
እራበኝ

ድሮ እኔናእናቴ ሲርበን

ብዙ አሳልፈን

ዛሬማ እየበላሁ እራበኝ

ርሀብ የ9ወር እድል መሰለኝ

አስፓልቱን፣ጥጋጥጉን

ስመለከት ይርበኛል ግራገባኝ

ላለማየት መነፀር አረኩኝ

ልቤ ድምፅ አየሰማ

ያይኔ ቀረና በልቤ ተራብሁኝ

እስካሁን....

እየበላሁ፣እየጠጣሁ፣

እርሀብ የሚጮህብኝ፣የሚያድርብኝ

የብርሀን፣መንገድ ርሀብተኛ ነኝ።አኮረፋኩኝ

ባለሁበት ተቀምጭ አስተዋልሁኝ

ግራ ቀኜን ዙሪያዬን አየሁኝ

የኔ የምለዉ ባለመኖሩ

እኔም አገሬ ላይ ነኝ

ብዬ እየተወዛገብሁ

ያ...የማነዉ ብዬ ጠየቅሁኝ

የሚመልስልኝ ሰዉ በማጣቴ

እኔም የምኖረዉ እዉጭ መሰለኝ

አኮረፋሁ....

ነገሮችን የሚያስረዳኝ ሳጣ

ምነዉ አላኮርፍ

እልሄ፤ብሶቴ አይመጣ

ከእናቴ በጎ ምላሽ ባጣ

ልቤ ይለኛል

ፈርጥጥ፣ሩጥ ካገር ዉጣ

ማኩረፋማ...

ያጠናሁት የተማርሁት

በራሴ ነዉ።

እንደስጋ እዉነት

ተከትፋ፣ተፈጭታ፣ተቁላልታ

ከራሴራሴ ነዉ ያየሆት።ሴራ

ለሰዉ ልጂ የማይራራ

ስንቱን አስወጡት ከሰዉ ተራ

ስንቱ ተነገደበት ተራ በተራ

ሴራን ባወቃችሁ....።

ተሞልቶ በወገን፤ላገር ማሰብማ

ድሮ ቀረ ከድሮዋ እማማ

ዛሬማ ለራስ ሆነ 

ቀረ ማሰብ ለእናት

ስልጣን ለሴክስ ዋለ

በሴራን ወገን እየታለለ

ሴቶች ስልጣን እያታለለ

ሴራ ብቻ ሆነ

ወንድ ልጂ የትም እንደቀረ

የወንድ ልጂ ስልጣን ድሮ 

ቀረ

ሴትም ወንድ ነች

ስሜት ሳይገዛት ለህዝብ

ከሰራች ካሰበች

ግና....

ዛሬማ ስልጣን ለስሜት መሆኑን

ወገን ምንኛ ባወቅን

ለእናት ሀገር ማሰብ

አብሮ መዉረድ ከአማረን

ሴራን ትተን ከአማረን

ህዝብ ወዳድ ከፋ ባደረግን።
ሾላ

ያ...የቤት በላይ አዉጋራችን

አድባራችን ካንተ ላይ ነዉ

ገና በመብቀልህ አብሮ 

ስታድግ ያደገዉ።

አይ ሾላ....

እዉነትም አድባር ነህ

ካንተ ጋር የበቀሉ ሁሉ

አፈር ለአፈር ከሆኑ

ብዙ እልፋ አመት አስቆጠሩ።

ከጥግህ ብዙ አሳልፈዉ እየጨፈሩ

ብዙ ሳይቆዩ ይሸመግላሉ 

ከዚያም ይሞታሉ

አንተግን አድባር ነህ

ሁሉን እንደ ቸርነቱ ትይዛለህ


ወቅት ጠብቀህም ታፈራለህ

ያን ግዜ ይመገቡሀል

በሩቅም ሲያዩህ ይለዩሀል

ሰፈራችን እያሉ ይጠቋቆማሉ

ያዩሀል ከርቀት እያስታወሱ

የመገብሀቸዉን ፋሬ እያወሱ

አድባር ሆነሀል ሾላ በመሆንህ

ሰዋች ይጠሩሀል ሾላ ብለዉ

ከስርህም ተቀምጠዉ እነአበዉ

ተረት ተረት እያሉ ያወጋሉ

በስርህ ልጆች በላይህ ላይ ወፋች 

ይንጫጫሉ:

ደስ እያልሀቸዉ መላ አካልህን

እያዩ።


ነገር

ከዩንቨርስቲ ነገር ተምሬ

አትፋረዱብኝ ቁስል በመነካካቴ

እኔም በነገር ቆስዬ ነዉ

በብቸኝነት ወገን ያጠናቀቅሁት

ግዜዉ ለብቸኛ ወገን ላላስከተለ

መቼ ጠቀመና አገለገለ።

ነገር ልምከርህ....

በየትም ቦታ ወገን ካላስከተልህ

የምትወደዉ ጎደኛህ ይከዳህ

የምቀርበዉ ሰዉ አዉሬ ይሆንብህ

ያንጊዜ ነገር ይገባሀል ዉሸት

ሁሉም ሲኮንንህ ሲያናድድህ

ከዚህም ሌላ ምሁር ብኮን ያጣጥልህ

እኔም ተማርሁ....

ወገኔ በሌለበት ከዩንቨርስቲ

ወገኔ ሁሉም ነዉ በማለቴ

ያንዩ ገባኝ ወገን እንደሚያስፈልግ

ስለዚህ ነገር ሳትማር ወገንህን ፈልግ።

ጥሩ ደረጃ ለመድረስ በወግ በማረግ።

ሙስና

እኛ ከታች ያለን

ስንተች ስንዋረድ ሰንብተን

ሙስናማ በፈተና ከታላላቆችን

ተማርን ተማረርን

ጂብ በቀደደዉ ዉሻ ይጮሀል

ከተባለ ብለዉ

የኛ ሚዲያተኛች አራገቡት አሉ

ማራገብ ብርቅ ነዉ እንዴ

እኛስ ከልብ ከእዉነት ያጣነዉ 

ሙሰኛዉን

እናሙስናን ለይቶ የሚያሳይ ነዉ።

መምህር

የእዉቀት,እናት

ነዉ

የእዉቀት ጀንበር

የሚያሞቅ

የእዉቀት ቀለም ነዉ

እዉቀቱን በእኩል የሚያካፋል

እኔ የማዉቀዉ መምህር

እንደዚህ ነዉ

እኩል ለሁሉም የሚለግስ

ግና......ግና

ተማሪዉን እኩል ካልመዘነ

ያንግዜ ነዉ በዩንቨርስቲ ማዘን

ያን ግዜ ነዉ መማር የሚያስለቅስ

መምህር...ከዚህ ይለያል

መምህር እናት ነዉ

በእዉቀት የሚያሳድግ

ከእናትም በላይ ሰሪ ነዉ

ገና ከ ሀ..ሁ..ብሎ ላስቆጠረዉ

ለኔ መምህሬ....

ይለኝ ነበር ተመራመር

እኔም በሀሳቡ ተስማምቼ

ስመራመር ሳጠና ቆይቼ

እድሜዬን አሳለፋሁ 

ድግሪ አመጣለሁ ብዬ 

እንደባልደረቦቼ

መማር መመራመር ለህይወት

መሆኑን ትቼ ለደመወዝ አረግሁት

ለመኖር ደመወዙን

ደመወዙ እያጠረ አልበቃ አለኝ

መምህር....

መምህር ስጦታነዉ

ላወቀዉና ለታደለዉ።

እግሮች

አግሮች ባይኖሩ፣ባይሰሩ

ጀግናዋች ባልነበሩ

ስንቱ ያገሬ ጀግና 

ገበናዉም ይሆን ነበር መና

እግሮች በመኖራቸዉ.....

ስንቱ የከፋዉ ፈረጠጠ ሮጠ

አሻፎረኝም ያለ አመለጠ

እስራት እግሮቼ አላስተማሩኝም

ብሎ እግሮቹ እንደተራመዱለት

እየሮጠ እየፈረጠጠ

እግሮች....

ከመሮጥ መፈርጠጥ ይበልጣል

መፈርጠጥ በእግሮች አይሳካም

ለዘላለሙም ዉጤት፣አያዋጣም

እግሮች....

አንገት አያስደፍም በመሰረቱ

እንደሚባለዉ ከፋትፋቱ ፌቱ

ከፈለግህ ያበራሉ ያከንፋሉ

ልዩነቱ አጠቃቀሙ ነዉ

አስተዉሎ ጥቅሙን ላየዉ

ቤተሰቦቼ ካላልህ ከበረርህ

ሌላዉ ይቅር ሩጭ ትሆናለህ

እግሮች ብቻቸዉን ዋጋ የላቸዉ

ቁምነገሩ ከልብ ጋር ነዉ

አብረዉ ሲሰሩ ሲሰሩ ነዉ።

ልብ

ሰዋች ልብን በፍቅር ይመስሉታል

ለኔ ግን ይለያል

ልብ የሀሳብ ዉጥን ማደሪያነዉ

ሀገር የሚገነባዉ የሚፈርሰዉ

በልብ ስራ እኮ ነዉ።

ልብ እንደመሪዉ ነዉ

መጥፎ እንስራ ካሉት ይሰራል

ደግም ሁን ካሉት ይሆናል

ልብማ እንደዉሀ በመሩት 

ይዘምታል ይጎዛል

ልብ እንደ መሪዉ ነዉ

ዉጤት እና ሰኬት የሚኖረዉ

ጀግና ልሁን ብለህ ልብን 

ከመራሀዉ

ጀግና ትሆናለህ

ልብ እንደሰሪዉ እንዳስተዋዩ ነዉ።
ሀገር

ሀገርማ ሰዉ ነዉ

ሀገርማ ተራራ፣ሸንተረር ነዉ

ሲያርሱት የሚታረስ

ሀገር ማለት እኮ....

የእትብትህ መቀበሪያ

የምጠጣዉ ዉሀ መመንጫ

የትዳር ዉጥን መጀመሪያ

ሀገር እኮ....

ከልጂነት እስከ እድገት

ጣፋጭ ህይወት ማሳለፌያ

በመጨረሻም የህይወት ማረፌያ

ሀገር እንዳያይዙ ነዉ

ብልጥ ሆነህ ካልፈጠንህ

ሀገር ይመርሀል፣ያስጠላሀል

ሀገር ህይወት፣አይን የለዉ

መጥፍዉን ከደግ የሚለይበት

ሀገርማ ሀገር ነዉ

ሀ.....ገ......ር....


አያገባህም አትበሉኝ

የሽሬ ልጆችን እወዳለሁ

ሀገር እያሉ ሰማሁ

አንተ ምን አገባህ

አትበሉኝ 

ለሀገሩ የሚጠራ ሰዉ

እወዳለሁና።


ገዢና ተገዢ

ማንና ማናቸዉ ገዢናተገዢ

እንደባሪያዉ አሳዳሪ ፈርኦን

ተገዤዉ ማነዉ ስፓርታከስ

ለነፃነቱ ትግል ያደረግ

ካልታገለማ የዛሬዉ ስፓርታከስ

መቺታዉቆ፤

ባይታገል ስፓርታከስ ልጆቹም

ባልታገሉ፣

ስዋች ነፃነት በትግል መሆኑን

ባዋቁ

ህይወትም ይለያል በገዢና ተገዢ

ላሳያችሁ የፈርኦንን አወዳድሪ

ልዩነቱ ከስፓርታከስ ግልፅነዉ 

ገዢና ተገዢ ያዛሬን ቆሞ ላየዉ።

ዛ.....ሬ....ማ....

ቀለም ለዉጧ አላዩት

እነስፓርታከስ

እንደነሱ ያለ ታግሎ በወጣለት

ትምህርት ከወሰዱ ከስፓርታከስ

ያንግዜ ይገባቸዋል ስፓርታከስ

ያንግዜ ይገባቸዋል

ገዢ ና ተገዢህልም አለኝ

ያ ወገኔ በወሬ ሳይሆን

በሀይል ጠላቱን አንበርክኮ

የማይ የማስተዉልበት።

ህልም አለኝ፤

ወገኔ በይምሰልን ትቶ

ከወደቀበት ቦታ ቀና የሚልበት

እዉነት እንደመሸ የማይቀርበት

አዋ እኔ ብኖርም ብሞትም

በዉሸት የጨለመዉ

መንጋቱ መነሳቱ አይቀርም

ያንጊዜ ህልሜ ይሳካ ይሆናል

ግን እስከዚያዉ ልተኛ

የወገኔ እንባ ካልተኛሁ ይደርቃል

ህልም በእንባ ነዉ

እዉን የሚሆነዉ 

አይ ወገኔ....

ጎበዝ በርትቶ ካልገፍ

ሴትኛ አዳሪነት ምንኛ ይስፋፋ

ጠላቴ የወገኔን ብልት ያለፋ

ህልም አለኝ....

ወደፌት ይነጋ እየመሰለኝ።ማነኝ?

የእድገት ወሪ የማይገባኝ

ሀቅን ያነገብሁ አርማ

ለይምሰል መኖር የማይገባኝ

ማንም ሀሳቤን የማይከለክለኝ

በተግባር የማሳይ

እኔም እንደናንተ የተወለድሁነኝ

አረ እኔ ማነኝ

የሰዉ ሴራ የሚገባኝ

በእዉነታ፣በሚዛናዊነት የማምን

ለወገን የቆምሁ የምኖር

ወገኔ ወድቆ ሳይ የማልወድ

ወገን ወዳድ የሆንሁ

እኔ ነኝ

አረ እኔ ማነኝ።

ያልበላም ይኖራል።

ይኖራል

በዚያ በናንተ ሰፈር

አላያችሁም ተደፋቶ የሜኖር

ሌላዉ ይቅር የወደቀስ

አዋ...ልናገር

በዚያ በጥጋጥጉ በአስፓልቱ

ያልበላ ይኖራል ቢባልም

ቢሂሉ....

የነሱ የተለየ ነዉ

ርሀብን ለብሰዉ 

ዉርጬን አገልድመዉ

ያልበላ ይኖራል....

ባልጠፋ ሀገር ተጨንቀዉ

እንዴህ ምነዉ ሆኑ

እነ አ...በ....ዉ.....

በመጦሪያ መሰናበቻ እድሜያቸዉ

ይህም ይ....ቅ....ር......

እነ ፈላዉ፣ጬጫዉ ሎጋዋ

ምነዉ መሰቃየታቸዉ እንዳይዋ

ያልበላ ይኖራል በሏ

አዋ ያልበላ ይኖራል

መአድ የማያዉቀዉ

እስቲ እኛ ከበላን

ያልበሉት ያልበሉትን አያችሁ

አላልሁም ያልበላም ይኖራል

አይታወቅም ያልበሉት 

ይነሱ ይሆናል።


ታሪክ

ስንቱ ሲያወራ ሲተርክ

ታሪክ ነበረን እያሉ

በዋዛ አመታት አለፋ

እየለፈለፋ....

ሰርቶ መገኘት ነዉ

ፋሬ ታሪክ ያለዉ

ምን ኮነ ሰው

መስራት ለመኖር ሆነ

በታሪክ መኖር ባመነ

ታሪክም መኖር ነዉ

ታሪክን በልቦናዉ ላየ

ወጣቱ ተስፋዉን አላየ

በልቶ መኖር ዋጋ የለዉ

ታሪክማ...

ከዚህ በተቃራኒ ነዉ

ብዙ መፀሀፋም መፃፋም

ታሪክ አይደል

ብዙ ብዙ ነገር

ታሪክ አይደል

ታርክ ነፋስ አለዉ

ለወደፌት ትዉልድ የሚያስተላልፈዉ።

አማሪኛ

ስንቱ አገባሽ ሞሸረሽ

ስንቱ ነገደብሽ ገዛሽ

አይ አማሪኛ....

ስንቱን ስንቱን አሰማሽን

ለኛ የቆርቆሮ ሆነሽ

በመላላትሽ ለገዤዋች ወርቅ

ሆ....ን....ሽ

አዋ! ቆየሽ....

አይ አንቺ አማሪኛ!

ስንቱ ፈዘዘ ባንቺ ዋጋ

ስንቱስ ቀረ ዋጋ ሳዋጋ

እረ እኔ ልመስክር

አንች የሆንሽ ለገዢነዉ

አንቺን የሸጡማ የታሉ

እነሱ በተስፋ ይጠናሉ

ጨለማዉ አልፋ ቀን ይመጣል

እያሉ

በዚያዉም እኛም አማሪኛን

እንደፈለገን እናደርጋታለን እያሉ

አሁንማ ይሸጣሉ

አማሪኛ አማረን እያሉ።


ተስፋ

የወደፌት ህልም ማሳያ

የህልም መጎዦ መሳሪያ

ከጨለማ ወደ ብርሀን

መጎዧ

ይባላል አበዉ ሲተርቱ

ግና ኢትዩጲያ ሆኖ

ግና እዚህ ሆነን

ስንቶቹ ናቸዉ ያየን

በተስፋ ብቻ ያኖሩን

የኖርን

ተስፋ አዲስ አይደለም

ለኔ እናት ሀበሻዋች

አይ ተስፋ....

ስንቱን አስሮ አኖረ

ስንቱስ ....አማራረ

ከዛሬ ነገ ይነጋል እያለ

ሌሎችም አሉ

ተስፋ ብቻዉን አንፈልግም

ብለዉ ዉስጣቸዉን ያለሙ

ብዙ ጉርጉር ያነሱ

ጉርጉራዉስ ይበልጥ ለብልጥ

ከበረቱ ለወገን የሚያሳልጡ

ተስፋ....

እንደ ባለቤቱ ነዉ

አተኩሮ ለተመለከተ ና ላየዉ

ተ...ስ....ፋ

የልጂነት ፋቅር።

የጥንቅሽ እሸትና 

የልጂነት ፋቅር

ሁለቱ አንድ ናቸዉ።

ካለፋ በላይ የማይገኙ 

የ...ል...ጂ...ነ....ት

መዉደድ ሆነ ፉቅር

ፋት ፋት ነዉ እንዳይመር

ካጠበቁት መመኪያ ይሆናል 

ካላሉት የትም ይቀራል

ፉቅር እንዳያያዙ ነዉ

በህይወት መቼም 

አይረሳ

ከላይ ነዉ የልጂነት

የያ ንዬ ጊዜ

መቼም የማያቀረቅር

የልጂነት ፋቅር።ጭንቅላት ቀፋ ነዉ።

አዋ....

ጭንቅላት ቀፋ ነዉ

ለተጠቀመበት ማር መስሪያ

ላልተጠቀመበት ህሌና መበረዧ

ሆላ ቀር ሀረግ መበስበሻ

ጭንቅላትም እንደዚህ ነዉ

ለጥሩ ሰዉ ጥሩ ሀሳብ መብቀያ

ለመጥፋ ሰዉ ሀሳብን ማበስበሻ

ከዚህም ሌላ....

የመጥፋ ሰዉ አፉ ሲከፈት

ይሸታል የጭንቅላቱ ዝቅተት

ጭንቅላት ባዶ ነዉ

አዋ ጭንቅላት

ለጥሩ ጥሩ ነዉ

ካልተጠቀሙበት 

ጭንቅላት ባዶ ነዉ።

አዋ....

ከልተጠቀሙበት

ጭንቅላት ቀፍ ነዉ
ሰዉ ለምን ይሰክራል?

ህሌናዉን ማሸነፋ እየቻለ

ሰዉነቱን አጠንብዞ እያነሆለለ

ሰዉን ያስቀይማል 

ያዙኝ ልቀቁኝ በድንዛዜ እያለ

ሰዉ በሲጋራ፣በመጠጥ ደንዝዞ

መኖር ከጀመረ ያንዬ ነዉ መርዶ

መደንዘዝ፣መ...ጠ...ንበዝ

ያመጣል፣ያደርሳል ብ...ዙ መዘዝ

ሰካራ...የህሌና ደንባራ

ስካር ብዙ በብዙ ሲደራ

ያንዬ ነዉ የጠነበዘ ሰካራ

ይህን እያወቀ ሰዉ ይሰክራል

አ...ል...ገ...ባ....ኝ.....ም

ሰዉ ለምን ይሰክራል(2)

የሰዉ ተቃራኒነኝ

አዋ ተቃራኒ ነኝ

ሰዉ ሲዝናና አልወድም

ትንሺ ቅናት አለችብኝና

ጎደኛቼ ሲጫወቱ አልወድም

እኔ ጨዋታ አልችልምና

ሲፋቀሩ ማየት አልወድም

እኔ ማፋቀር አልችልምና

ሰዋች ሲኖሩ አልወድም

እኔ መኖር አልችልምና

አዋ እኔ ተቃራኒ ነኝ

እኔ እንደነሱ አልችልምና
ህልሜ አሰቃየኝ

በጉዟ ላይ ሳለሁኝ

መኪና መጥቶ ልዉሰድህ

ብሎ ሲጠይቀኝ ግራ ገባኝ

ጭነት መኪና ነበርና ከላዪ ላይ 

ወጥቼ 

አገር አማን ብዬ ተቀመጥሁኝ

ከዚያማ ፋጥነቱ ቅፈቱ

በጣም በጣም አስጠላኝ

ቀስ ብሎ እጂ እግር የሌለዉ

ሰዉ ሆነ በጣም ፈራሁኝ

ይህ ብቻ መይ በቃ

መኪናዉ በመጣ ቁጥር

ከልቤ በጣም ተሳቀቅሁኝ

ከሚያስፈራኝ እሱ አንዱ ቢሆንም

እባብ እፈራለሁ በየመሬቱ ሲጋደም

አስታዉሳለሁ በባምብ ተመትቼ

ስወድቅ ራሴን ስቼ

አረ ማይዳኘኝ ወገኖቼ

እየኖርሁ በህልም ተሰቃይቼ።አላዉቅምና አስተምረኝ።

ሳይኮሎጄ እያልህ

ከልብህ ሳኮን ስታስረዳኝ

ብዙ፣እንታ ፈንቶ እያልህ 

ከልብህ ሳይሆን ከአንደበትህ

በሳይንሱ ፈገግ ብለህ ብታስረዳኝ

መቼ ገባኝ አፋር የሆነ አለኝ

እንዴትስ ይግባኝ ከልብህ ያላየሁትን

አዋ አይገባኝም

ሲገባህ ያንዬ አስረዳኝ

እኔማ እኔነኝ አንተ አታዉቀኝ

እኔ ራሴን ላስተዋውቅህ

መጀመሪያ ታሪኬን ልንገርህ?

አዋ አንተም አፈር ነህ

እኔም አፈር እንዳንተ ነኝ 

ልዩነትም በትክክል አለን 

አንተ አፈር ነህ

እኔም አፊር ነኝ

ልዩነቱ አንተ ብዙ አፈር ነህ

እኔ ግን ብጥጤ አፈር ነኝ

አይገባኝም አረ የሚያስረዳኝ

አይገባኝም፣አይገባኝም

አዋ አይገባኝም ሳይንስ
ልቤ ተሰረቀ።

ማንም የማያዉቀዉን ልቤ

ዛሬ ተሰረቀ ከነቀልቤ

ቀልቤ ተሳበ ከነሀሳቤ

አረ...አማክሩኝ

ምን ይሻለኝ ንገሩኝ

አስረዱኝ ዛሬ እሰማለሁኝ።

ያኔዬማ ማንንም አልሰማ

አላማ የለ ሀሳብ

ሁሉም በላይበላይ ተሰረቀ

በሰዉ ሀገር ሆኜ

ምነዉ መሰረቅህ ሀሳቤ

ሀሳቤ መልስ እንጂ

ብዬ አንጀቴን ብጠይቅ

አሰተማረኝ ለራሴ መንቀጥቀጥ

አንተስ ተወዉ ልቤ ተናገር

ብዬ ብጠይቀዉ ሲናገር

ገባኝ እንደተሰረቀ 

አረ...ምክር ስጡኝ

መኖር እንዴት እችላለሁ 

ሳይኖረኝ ልብና ሀሳብ

አዉነት ግራ ይገባል

ያለልብ ና ሀሳብ መግባባት

ሌባ...ሌባ የልብ ሌባ

ማንን ልወቀዉ የልቤን ሌባ

ልቤ ና ሀሳቤ ተሰረቀ

መቼ አወቅሁ ሌብነት

እንዲህ በልብ እንደረቀቀ።

ስልጠና ዉጤት ይኑረዉ

መሰልጠን፣ብቻዉን ዋጋ የለዉ

አዋ እርግጥ ነዉ

ሁላችንም እራሳችንን ለማስተዋወቅ

እንሩሩጣለን ስማችንን ለማሳወቅ

ግን ሌሎችም አለን

የ ጋዜጠኝነትን ህግ ያከበርን

ይህ ብቻ አይደለም

በዜና አፃፅፋ፣በ ካሜራ አነሳስ

ስንታችን ከስልጠናዉ ተነሳሳን

ስንታችን በስልጠናዉ 

እዉቀት ገበየን፣አወቅን

ስልጠናዉንም ለዉጤት አዘጋጀን

እዉነቴን ነዉ በብዙ ነገር

ለዉጥ ቢኖረንም

ገና ብዙ ዉጤት እናያለን

ከስልጠናዉ የተገኘዉን ቀምረን

እኔ ግን ስጋቴ

ካሜራ ማን እና ሪፓርተሩ ላይ

በህብረት ካልሰሩ በጋራ

ስራዉም ቢሰራ አይጠራ

ካሜራ ማኑ ቀጠሮዉን ከተወ

ሪፓርተሩ በአግባቡ ካቀረበ

ሙያዉ ይመጣል እያበበ(2)
ይመስገን ብያለሁ።

ይመስገን ባይሉህ ይመስገን በላቸዉ

ምናልባትም ባልጋላይ እንዳሉ

እስከ ወዲያኛዉ ማሸለብ አለና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ድንገት ህይወት ያልፋል እና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ከኔ በታች ብዙ አሉና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

በህይወቴ መሰናክል አልፌያለሁና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ከስራ ዉዬ ገብቼ አለሁና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

በህይወቴ ስቃይ አይቻለሁና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ከበሽታ ድኛለሁ እና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ስተኛ ህልም አይቻለሁና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ተመስገን የሚባል ሰምቻለሁና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ከጎደኞቼ ተጣልቻለሁ እና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ሁሉን በአይኔ አይቻለሁ እና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ለፉቼ ሰርቼ በልቻለሁ እና

አሁንም ተመስገን እላለሁ

ወደፌት እሞታለሁ እና

ተመስገን ማለት አይከፋም

ብዙ የሚከፋ አለ እና

ተመስገን ይሻላል

ሌላም ሌላም አለ እና

ተመስገን ...ተመስገን***ሀቀኛ እስካገኝ እጠብቃለሁ***

አምነተኛ በስራዋ የምኮራ

በሀብት በዉቀት የማትኩራራ

የኔ የሆነችዉን ወርቄን እስካገኛት

እጠብቃለሁ በፅናት በፀሎት

ደግሞም የሷ እዉነት

ለኔ ወርቂ ናት

እዉነት እዉነት ጠብቃታለሁ

እሷን ለፋቅረኛ ለህት

አሁንም እጠብቃታለሁ

ትመጣለች ብዬ ተስፋ አረጋለሁ(2)
ሰዉ አልችልም ይላል።

ጥሩ ደረዳ መድረስ

እየቻለ አልችልም ይላል

ሳይሰራ እያሰበ ይደክማል

ዝም ብሎ በሀሳብ ይበራሉ

ከዚያም ተስፋ ይቆርጣል

ከዚያም እራሱን ይጥላል

ከዚያም እሞት ይመስለዋል

ከዚያም በቅየት ይኖራል

ከዚያም መስራት እየቻለ

አረረ.....አልችልም

አዋ እኔ.....አልችልም

አዋ መስራት አልችልም

ይላል ከልቡ አዉጥቶ።


ሞት ለሁሉም እኩል ነዉ።

ሞት እኮ አያዳላም፣

ሞት ድሀ፣ሀብታም

ቆረቆራም ሆነ እከካም

መላጣ ሆነ ሽበታም

ምሁር ሆነ ችስታም

ጭባ ሆነ ጉልበታም

ጤነኛ ሆነ ዱቃቃናም

ምርጥ ሆነ ቀሽታም

ሞት በዚህ አያምንም

ሁሉንም በእኩል ይሸኛል

በሞት ሁሉም እኩል ነዉ

ደሞም ካሰበበት ሞት የዋህ ነዉ

ለሁሉም እድሜ ይሰጣል

አይ ሞት ለድሀ አስደሳች

ለህልመኛዉ ጭጎጎት

ሞት የእኩልነት

ፅዋ ምልክት

ህህህ....

ሞት ሞት ነዉ

ለሁሉም ፍጥረታት።ዜና አንተን ለመጣላት ብዙ ምክንያቶች አሉኝ።

1,2,3,4..1000,4000....1000,000,000,000

ምናለበት አጠር መጠን ብትል

እንደዚህ እንዳየሁህ ሁለት ገፅ ባሞላ፤

እንዲህማ ከሆንህ ዜናነትህ ቀርቶ

ወሬ አለያም ተረት ትሆናለህ

ምን ያንተ ጉድ ማለቂያ የለዉ፣

ከለይህ ላይ ስዉስት መስመር

አርስተ አንቀፅህን ደምረህ

በዚያ ላይ መቺ እንዴት ለምን

በማን የመሳሰሉትን ሳታካትት

ምን ዜናነህ?አረ...አጠር...አጠር

ምን ማጠር ብቻ ግልፅ ሁን እንጂ

እኔ አንተን ለመተቸት ብዙ ብዙ ምክንያቶች አሉኝ፣

ላሁኑ ይህን ብዬ ልለፋህ እንጂ።

ምርጥቃል፣የያዝህ፣ግልፅ ሁን

ዉሸት፣ግነት ከሞላብህ

አንተ ዜና አይደለህም ወሪ እንጂ

ሚዛናዊ፣ግልፀኝነት ከሌለህ

አንተም ዜና አይደልህ

እኔ አንተን ልተች ብል

ብዙ...ብ...ዙ

እንከኖች አሉብህ ዋና ዋናዋቹን

ዘረዘርሁልህ፣ነገርሁህ እንጂ

ለዛሬዉ ይበቃል እኔም ላስብበት ።


ዛሬ ና ያንዬ።

ያንዬ ፌስቡክ በሌለበት

እንተርኔት በጠፋበት

ፍቅር ከነካባዉ በደራበት

መዉደድ በማይሸራረፋበት

ድር ነበር ጌዜ

ሁሉ የሚተማመንበት።

ዘንድሮ ማ...ጊዜ ነዉ?

ሚስት ባሏን አስቀምጣ

ልቧ የሚሰረቅ

ፌስቡክ ባመጣዉ ጣጣ፣

ባል ፋቶ በፌስቡክ አይቶ

ተጥዶ ይዉላል ከጠዋት አንስቶ

ልጆች ትምርት ትተዉ

በፌስቡክ ሲያወሩ ይዉላሉ

ከትምህርት ሲወድቁ

ብዙ ነገር ያመሀኛሉ፣

አረ...በፌስ ቡክ

ስንቱ ገባ ጭንቀት

ስንቱ ጨለመበት

አይ....ድሮ ና ዘንድሮ


ሰዉን እንዳሰማ!

ደግ ብትሆን 

ሞኝ ነዉ ይሉሀል፣

ለብሰህ ካማረብህ

ከአንተ ጋር 

አይሄድም ይልሀል፣

ለብቻህ ብትቀመጥ

አዘንህ ተከዝህ ይሉሀል፣

ከጎደኛህ ጋር ብኬድ

ዘረኛ ነዉ ይሉሀል፣

ስራህን ብሰራ

ቆምጭ ነዉ ይሉሀል

ቡና ብጠጣ ሱሰኛ

ነዉ ይሉሀል፣

ብትጫወት ወሬኛ

ስራፈት ይሉሀል፣

አረ...ሰ...ዉ

ብዙ ብዙ ይሉሀል፣

ምን ይህ ብቻ

ጨዋታ ከቻልህ

ሞኝ ጂል ነዉ

ይሉሀል።

ፋቅረኛህን ካቀፋህ

ሸሌ ነዉ ይሉሀል፣

ዝም ብትል ፈዛዛ

እንቅልፋም ነዉ

ይሉሀል፣

አረ...ሰዉን እንዳሰማ

ሰዉ ሞተህ እንኮን

ብዙ ብዙ ይልሀል፣


እኔ የምለዉ!

ያንዬ ልጁ ሆነን ሳናዉቅ

የምንሰራዉን ቆም ብለን

አስበን፣አስተዉለን እናቃለን

ስንቱ ከጎናችን ተነስተዉ

ጠንክረዉ በመስራት፣በመሮጣቸዉ

ሰንቶቹ ከሩጫዉ መቋጫ ደረሱ

ስንቶቹ ከመንገድ ላይ ቀሩ

ስንቶ ከዉድድር ወጡ

ስንቶቹ ሀሳባቸዉን ቀየሩ

ስንቶቹ...ብዙ ብዙ ሆኑ

ልጁነት ወርቅ ነዉ

ልጁነት ሀብት ነዉ

ከእዉነት ላወቀዉ ለተረዳዉ

የልጂነት ጊዜ መሰረት ነዉ።

ለወደፌት ህይወት መሰረት

የደስታ መኖሪያ ቤት

የህይወት ሀሴት መገብያ

የሰዉነትህ መጠለያ ቤት

ከልጁነት እስከ ትምርትቤት

መሰረት ነዉ ልጂነት ለህይወት።ያ፣አንዳንድ ህልም!

እየሮጥህ ሳደርስ

ዳገት እየወጣህ ሳደርስ

ብስጭትህ ሲበዛ

በመራራ ሀዘን ተዉጠህ

የሰዉ ፋቅርህን

ለማየት ካልታደልህ

ችግሩ ካንተ ነዉ።

ፀሎት፣ፀሎት

ይቀርሀልና።

ይህን አድርገህ

ካልተሳካልህ

ችግሩ ያንተ ነዉ

ነፋስህን እረፋት አልሰጠህምና።

Ad blocker interference detected!


Wikia is a free-to-use site that makes money from advertising. We have a modified experience for viewers using ad blockers

Wikia is not accessible if you’ve made further modifications. Remove the custom ad blocker rule(s) and the page will load as expected.